ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
በ2011ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥር 13 እና 14 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ጥር 15 እና16 ይሆናል፡፡
በምትመጡበት ጊዜ፡-
· የ8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ኦሪጅናልና ኮፒ፣
· የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ዉጤትና ትራንስክሪብት ኦሪጅናልናኮፒ፣
· ስምንት ጉርድ ፎቶ ግራፍ 3×4 የሆነ ፣
· አንሶላ፣ ብርድልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት