

ስልጠናዉ ከየካቲት 18-19/2014 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ በሚገኘዉ ትልቁ ኣዳራሽ የተከናወነ ሲሆን ፤የተለያዩ የሥራ ክፍል ዳይሬክተሮች߹የኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም ሌሎች ከግዢ ሂደት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸዉ ክፍሎችን ያካተተ ነበር፡፡በሁለቱ ቀን ቆይታ በመንግስት ግዢ ምንነት߹እቅድ ዝግጅት߹ ዘዴ߹ዑደት߹በቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ አዘገጃጀት߹በመደበኛ የጨረታ ሰነድ ይዘት እና አጠቃቀም ወዘተ ላይ ያተኮሩ ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል ፡፡የስልጠናዉ ተሳታፊዎችም በቂ ግንዛቤ በማግኘታቸዉ በግዢ እቅድ ዝግጅት߹በግዢ ጥያቄ አቀራረብ እና በጠቃላይም የግዢ ሂደቱን ዑደት በትክክል ተረድተዉ ተቋሙ የሚያከናዉናቸዉ ግዢዎች ግልፅ߹ቀልጣፋ እና እንከን አልባ ይሆኑ ዘንድ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚጫወቱ ገልፀዋል፡፡