ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም. መደበኛ የቅድመ ምረቃ መርሃ -ግብር ተመራቂ ተማሪዎች በስራ ፈጠራ ክህሎት ማዳበር ላይ ያተኮረ አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የካቲት 25 እና 26/2014 ዓ.ም መስጠቱ ተገለጸ፡፡
ስልጠናው በዩኒቨርሲቲው ደሊቨሮሎጂ ዩኒት እና መሃበረሰብ አገልግሎት ደይሬክቶሬት በጥምረት የተዘጋጀ ሲሆን በቁጥር ከ158 በላይ የሚሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች መሳተፋቸው እና ከነዚህም መካከል 29 በመቶው ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማም ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በቀሰሙት ዕውቀት እና ባካበቱት ክህሎት ላይ ያላቸውን ዝንባሌ አክለው በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም በስራ ፈጣሪነት ላይ አዎንታዊ አመለካከትን አጎልብተው ከተቀጣሪነት ወደ ቀጣሪነት መንፈስ በመሸጋገር እና የተሻለ ገቢ በማመንጨት እራሳቸውን ብሎም አገራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንዲችሉ ለማገዝ መሆኑ ተገልጿል ፡፡
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና የውጪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
የካቲት 26/2014 ዓ.ም.