ሴት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዉ ቆይታቸዉ የሚገጥሟቸዉን የተለያዩ ችግሮች ተወያይተዉ የሚፈቱበትን ሁኔታ ከማሳለጥ ኣንፃር ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በማሰብ የዩኒቨርሲቲዉ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ዝምታ ኪዳኔ ለሴት ተማሪዎች ተወካይ የቢሮ (የዜሮ-ፕላን ክፍል ) ቁልፍ ርክክብ ባከናወኑበት መርሃ-ግብር ላይ እንደገለፁት ፤ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚ አቅማቸዉ ዝቅተኛ ለሆኑ ተማሪዎች ከሚሰጠዉ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርታቸዉ ዝቅተኛ ዉጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች የማትጊያ ቲቶሪያል (tutorial) በየሳምንቱ ሦሥት ቀን እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
ወ/ሮ ዝምታ በዚህ የቲቶሪያል ኣሰጣጥ መርሃ ግብር በረካታ የተፈጥሮ፣የማህበረሰብ ሳይንስ እና የኣንደኛ ዓመት ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸዉ እና ጥሩ መሻሻል እንዳሳዩም ኣብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ዩኒቨርሲዉ ለሴት ተማሪዎች የሚሰጠዉን ሁሉን ኣቀፍ ድጋፍ ኣጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዉ በቁልፍ ርክክቡ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙትን ተጋባዥ ተማሪዎች ኣመስግነዉ ፕርግራሙ ተቋጭቷል።