ለኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

ማስታወቂያ

ለኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡

የ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነባር ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መስከረም 26 እና 27 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 28 እና 29 ይሆናል፡፡

በ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥቅምት 3 እና 4 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 5 እና 6 ይሆናል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ለምዝገባ በምትመበት ጊዜ ፡-

* የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውን (ኦርጂናል) እና ኮፒ
* የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤትና ትራንስክሪፕት ዋናውን (ኦርጂናል) እና ኮፒ
* ስድስት (6) ጉርድ ፎቶ ግራፍ 3×4 የሆነ እንዲሁም
* አንሶላ ፣ የስፖርት ትጥቅ ፣ የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር ጽ/ቤት

Scroll to Top